
ግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት ለገንዘብ ሚኒስቴር ተጠሪ ከሆኑ እና ሪፎርም ከሚተገበርባቸው የፌዴራል ተቋማት አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት የአገልግሎታችን የበላይ አመራሮች ለሪፎርም ስራው ትልቅ ትኩረት በመስጠት መርሐ ግብር ከማዘጋጀት ጀምሮ የቴክኒክ ኮሚቴ በማቋቋም፣ ለሪፎርሙ የሚያስፈለጉ ሰነዶችን በማዘጋጀት ወደ ስራ ተገብቷል፡፡ አገልግሎታችን ሰነዶችን ከማዘጋጀት በተጨማሪ ለሪፎርሙ ተፈጻሚነት አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡
በመሆኑም በዛሬው ዕለት ከፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የተዋቀረ የሱፐርቪዥን ቡድን በአገልግሎታችን በመገኘት እየተከናወነ ያለውን ሪፎርም ስራ የመገምገም እና የአካል ምልከታ አካሂዷል፡፡ ቡድኑም በአገልግሎቱ የተሰሩ ስራዎችን በማድነቅ በቀጣይ በተጠናክረ መልኩ መሰራት አለባቸው ባላቸው ላይ ሃሳብና አስተያየት ሰጥቷል፡፡ በመጨረሻም ቡድኑ የአገልግሎቱን የዲጂታል ስራዎች፣ የስራ ቦታ ምቹነት እንዲሁም የቢሮ ሁኔታን ምልከታ በማድረግ አጠናቋል፡፡